Sunday, August 13, 2017

የኑረነቢ ማህደር - አጭር ዳሰሳ


ከግርማ ጉተማ

የተስፋዬ ገብረዓብን አዲሱ መጽሃፍ "የኑረነቢ ማህደር" አነበብኩት። ቆንጆ መጽሃፍ ነው። መጽሃፉ በዋነኛነት ኑረነቢ በተባለ የሓልሓል ፋና መንደር ሰው (ኤርትራ) እና ቤተሰቦቹ እውነታኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ከመሆኑ ባሻገር ባሉፉት 130 ዓመታት በምስራቅ አፍሪካ የተከሰቱና ያካባቢውን ህዝቦች በብዙ መልኩ አፌክት ያደረጉ ማህበረ-ፖለቲካዊ ኹነቶችን በተለይም ከሰሜኑ ጫፍ እይታ (from Eritreans perspective) አንጻር የቃኘ በመሆኑ ብዙ አዳዲስ ነገሮችን አግኝቼበታለው።
.

አትላንታ ልዩ ነበር!!
ትናንት ቅዳሜ በአትላንታ ጆርጅያ የነበረው የመጽሃፍ ምረቃ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ። የኮሚኒቲው ሊቀመንበር ካሊድ ዩኑስ ለኔ እንግዳ ሰው አልነበረም። ብዙዎች ልጆቻቸውን ይዘው መጡ። ልጆቹ "ኦሮሚያ" የሚል ህብረ ዜማ አስደመጡን። ሲጨርሱ ደማቅ ጭብጨባ አዳራሹን አደመቀው። የጀግናው ባለራእይ የባሮ ቱምሳ ባለቤት ወርቅነሽ መጥታ ነበር። ታሪክ ጸሃፊው ፕሮፌሰር መሃመድ ሃሰንም ነበር። ዶክተር አስፋው በየነም ነበር። ብዙ አንጋፋ ስዎች ነበሩ። ብዙ ቄሮም ነበር። ዶክተር መሃመድ መሳጭ ንግግር አደረገ።

Friday, August 11, 2017

"The Nurenebi File" Now availebel On AMAZON


አማዞን ላይ ለሽያጭ ቀርቦ የነበረው"የኑረነቢ ማህደር" በማለቁ ሽያጩ ተቁዋርጦ መሰንበቱ ይታወቃል። ከዛሬ እለት ጀምሮ እንደገና ለሽያጭ መቅረቡን አሳታሚው አስታውቆኛል። መጽሃፉን ያላገኛችሁ አማዞንን ጎብኙ።
www.amazon.com